የማኅበረሰቡ አባላት በጋራ ሲሠሩ

መሠረታችን

ታሪካችን

ስለ አውራ አምባ ማህበረሰብ አዲስ ምዕራፍ ባህሪና ልማት ግንባታ ሁለገብ ማህበር

የአውራ አምባ ማህበረሰብ በመተሳሰብ፣ በእኩልነት እና እርስ በርስ በመረዳዳት የተሻለ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ባለው ራዕይ በ1964 ተቋቋመ።

የአውራ አምባ ማህበረሰብ በ1964 ዓ.ም በክብር ዶ/ር ዙምራ ኑሩ የሀሳብ አመንጭነት በተሰባሰቡ አርሶ አደር አባላት የተቋቋመ ሲሆን መነሻውም በ 5 መሰረታዊ ሀሳቦች ነው፡፡ (1) የሴቶች እኩልነትን ማክበር (2) የህጻናት መብትን ማክበር (3) በጤናም ሆነ በእርጅና ምክንያት ለስራ ብቁ ያልሆኑ ሰዎችን ማገዝና መንከባከብ እንዲሁም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ልጆችን በማሳድግ ማስተማርና ለቁምነገር ማብቃት (4) መጥፎ አነጋገርና አሰራርን ማስወገድ (5) የተበጣጠሰ ወገንተነኝነትን በማስወገድ ጥቅል ወገንተኝነትን ማጎልበት በሚሉ መሰረታዊ ሀሳቦች ላይ በመነሳት ተመሰረተ፡፡

ከ1964 ዓ.ም - 1977 ዓ.ም ድረስ በተናጠል በያለንበት ቦታ ሁነን ደካማ ወገን በሚኖር ግዜ በመሰባሰብ የዚያን ወገናችንን እርሻ በማረስ፣በመዝራት፣በማረም፣በማጨድና በመሰብሰብ በማገዝ እንዲሁም ከሁለት ግለሰብ ሰፊ ማሳን በመቀበል ማሳውን በመጠቀም እያመረትን ለዚሁ የበጎ አድራጎት አላማ በማዋል ምርቱን ለደካሞች በማከፋፈል ስናግዝ ቆየን፡፡

በ1978 ዓ.ም በህብረት ስራ ማህበር ብንደራጅና በጋራ ብንሰራ የበለጠ ደካሞችን ለማገዝ እንችላለን በሚል እሳቤ በህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተን በመስራት በትንሽ ጉልበት በርካታ ደካሞችን እያገዝን ስንሄድ የቆየን ሲሆን ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሁሉም አባላት አንድ-አንድ ብር በማዋጣት፤የሽመና ስራዎችን በመስራት የገቢ ምንጭ በማግኘት በራሳችን የውስጥ አሰራር ደካማ ወገኖቻችንን እያገዝን ቆይተናል፡፡

ከዚያም በኋላ የማህበረሰቡ አባላት ለረጅም ጊዜ ስንጓዝበት የቆየነው የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ ሂደትን ለማበረታታትና አቅም ያነሳቸውን ወገኖች በተሻለ ሁኔታ ለመደገፍ ይረዳን ዘንድ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ዕውቅና እንዲሰጠን ስንጠይቅ ቆይተን ጥቅምት 8/1999 ዓ.ም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የአውራ አምባ ማህበረሰብ አዲስ ምዕራፍ ባህሪና ልማት ግንባታ ሁለገብ ማህበር በሚል ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ እውቅናን አግኝተን በተቻለን ልክ ሰፊ ስራዎችን ስናከናውን ቆይተናል፡፡

አሁን ላይ ደግሞ ማህበሩ የበጎ አድራጎት ስራዎቹን በአገር አቀፍ ደረጃ በማስፋት ይህን የማህበረሰቡን መልካም ተሞክሮ በአውራ አምባ ብቻ ተገድቦ እነዳይቀር ለሌሎች በማድረስ በስራ እና በውይይት የሚያምን ትውልድ ለመፍጠር ይረዳው ዘንድ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 7406 በኢፌዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት ተሰጥቶታል፡፡ ሰፊ ስራዎችን ለመስራት ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡

የአውራ አምባ ማህበረሰብ አባላት ማህበረሰቡ ከተመሰረበት ጊዜ ጀምሮ በራሳችን የውስጥ አሰራር ማህበረሰባዊ የአብሮነት ኑሮ በመጀመር ለሰው ልጆች ምቹ፣ ሰላማዊና ፍቅር የሞላበት ኑሮ አስፈላጊ ናቸው ብለን ያመንባቸውን መርሆዎች አንድ ላይ ሆነን ደካማ ከጠንካራ በመደጋገፍ በመተሳሰብ፣ በመረዳዳት፣ በወንድማማችነት ፍቅርንና ሰላምን መስርተን፤ መጥፎ አስተሳሰብና አሰራርን አስወግደን መልካም አስተሳሰብና አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ በመሰረትነው ፍቅር ተደስተን ለረጅም ዓመታት እየኖርን እንገኛለን፡፡ ይህንንም ተሞክሮ ነው ለሌሎች ለማካፈል እና ተምረው ሰላማዊ ኑሮን እንዲኖሩ ለማስቻል ያሰብነው፡፡ ምክንያቱም የአውራ አምባን መልካም እሴቶች ወስደን ካልተጠቀምንባቸው ይህ አገር በቀል መልካም ባህል ወይም እሴት እንደ የጋን መብራት ሆኖ ይቀራል ማለት ነው፡፡

ያከናወናቸውን ተግባራት ያንብቡ

ራዕይ

በጎ አስተሳሰብን፣ስራ ወዳድነትን፣መረዳዳትን፣ ዘላቂነትን እና ለሰው በጎ ማድረግን በትውልዱ ላይ ሰርጾ ማየት፡፡

ተልእኮ

የተለያዩ ስልጠናዎችን እና ድጋፎችን በማድረግ የስራ ባህልን፣ ስነምግባርን፣ፍቅርን እና መረዳዳትን በትውልዱ ላይ እንዲሰርጽ በማድረግ መልካም ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል

ልናሳካቸው ያቀድናቸው ግቦች

ዓላማዎች

  1. የሀገር ባለውለታ የሆኑትን አረጋውያንን መርዳት፤ መንከባከብ እና ቀሪ ህይዎታቸወን ተደስተው እንዲኖሩ ማስቻል፡፡
  2. ወላጆቻቸውን በሞት ያጡና ለችግር የተጋለጡ ህጻናት የትምህርት እድል እንዲያገኙ የሚያድርጉትን ጥረት መደገፍ
  3. በኑሯቸው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶችንና የቤተሰብ ኃላፊዎችን ፍላጎታቸውን መሠረት ያደረጉ የሙያና የንግድ ክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠት የስራ መጀመሪያ የሚሆን የገንዘብ ወይም የአይነት ድጋፍ በማድረግ ወደስራ ገብተው በመስራት የራሳቸውን እና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ እንዲያሻሽሉ ማገዝ::
  4. የአውራ አምባ ማህበረሰብን ተሞክሮዎችና መልካም እሴቶች ለህብረተሰቡ በስፋት በማስተዋወቅ መልካም ተሞክሮው ለሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች መማማሪያ እንዲሆን ጥረት ማድረግ
  5. የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ላይ በመሳትፍ እና በማስትባበር ተፈጥሮ የነበረችበትን ይዘቷን ሳትቀይር ለቀጣይ ትውልድ እንድትተላለፍ ማስቻል፡፡
  6. ሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኛች ላይ ያተኮሩ የማህበረሰብ ግንዛቤ ስራዎችን ማከናውን፡፡
  7. በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ችግሮች ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች እርዳታ ማድረግ
  8. ታመው መታከሚያ ላጡ ወገኖች የህክምና ድጋፍ ማድረግ፡፡

አምስቱ ዋና ዋና መሰረታዊ ሀሳቦች

የሴቶች እኩልነት

የሴቶች እኩልነትን ማክበር እና በሁሉም ዘርፎች እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ማረጋገጥ።

የህፃናት መብቶች

የህፃናትን የመማር መብት መጠበቅ እና በእንክብካቤ እንዲያድጉ ማድረግ።

አቅመ-ደካሞችን መደገፍ

በጤናም ሆነ በእርጅና ምክንያት መስራት የማይችሉ ሰዎችን መንከባከብ፤ እንዲሁም ወላጅ አልባ ህፃናትን ማሳደግ፣ ማስተማር እና ለስኬት ማብቃት።

መጥፎ አሰራርና አነጋገሮችን ማስወገድ

በራሳችን ላይ እንዲደረግብን የማንፈልጋቸውን መጥፎ አሰራርና አነጋገሮችን ለማስወገድ መስራት።

ጥቅል ወገንተኝነት

የተበጣጠሰ ወገንተኝነትን በማስወገድ እና አንድነትን በማስፋፋት፣ የወንድማማችነት ስሜትን ማሳደግ።

የጉዞ ታሪካችን

የመጀመሪያዎቹ ዓመታት (ከ1964 - 1977 ዓ.ም.)

በየአካባቢያችን በተናጠል እንሰራ የነበረ ሲሆን፣ አቅመ-ደካማ የሆኑ የማህበረሰብ አባላትን በእርሻ ስራዎች ለማገዝ እና የተመረተውን እህል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለማከፋፈል አብረን እንሰበሰብ ነበር።

የኅብረት ሥራ ማህበር ዘመን (ከ1978 - 1998 ዓ.ም.)

እ.ኤ.አ. በ1978 ቁጥራቸው በርከት ያሉ አቅመ-ደካማ ሰዎችን መርዳት እንድንችል በኅብረት ሥራ ማህበር ስር ተደራጀን። ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሁሉም አባላት አንድ-አንድ ብር በማዋጣት፤የሽመና ስራዎችን በመስራት የገቢ ምንጭ በማግኘት በራሳችን የውስጥ አሰራር ደካማ ወገኖቻችንን እያገዝን ቆይተናል፡፡

ሕጋዊ እውቅና (ከ1999 ዓ.ም. - እስከ አሁን)

ጥቅምት 8 ቀን 1999 ዓ.ም. ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ የሕጋዊ ሰውነት እውቅና አገኘን። መስከረም 6 ቀን 2024 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ.) ደግሞ በፌዴራል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ዘንድ በሕጋዊነት ተመዝግበናል።

የማኅበረሰብ ልማት ሥራዎች

የሕጋዊ ሰውነት ሁኔታ

የፌዴራል ምዝገባ

ድርጅታችን በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት የምንንቀሳቀስ ሕጋዊ አካል ነን። በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ዘንድ በምዝገባ ቁጥር 7406 ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም በሕጋዊነት ተመዝግበናል።

የአመራር እና የቦርድ አባላት

አቶ ሙሉጌታ ገብሩ

የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ

ወይዘሮ የምሥራች በላይነህ

የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ

አቶ ዓለሜ ሙሐመድ

ፀሐፊ

ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ

አባል

ወይዘሮ እናነይ ክብረት

አባል

አቶ ኑሩ በላይ

አባል

አቶ እንግዳው አገዝ

አባል

አቶ ሞገስ ኑሩሐቅ

ዋና ሥራ አስኪያጅ